የጉዞ ዋስትና ምንድን ነው?
የጉዞ ዋስትና ከኢትዮጵያ ውጭ ወደየትኛውም የአለም ክፍል ለተለያዩ ምክንያቶች የሚጓዙ ሰዎች ሊገዙት የሚገባ የውል አይነት ሲሆን ውሉ ላይ በተጠቀሰው መጠንና ሁኔታ መሰረት፡-
- ላልተጠበቀ ድንገተኛ የህክምና ወጪ ሽፋን
- ለድንገተኛ የአካል ጉዳትና ሞት ካሳ
- በጉዞ ላይ ለሚከሰት የሻንጣና የእቃ መጥፋት ሽፋን
- ለህጋዊ ተጠያቂነት የተወሰነ ድጋፍ
- ለጉዞ መሰረዝና ሌሎች መሰል ያልተጠበቁ ክስተቶች ሽፋን ይሰጣል
በሄዱባቸው አገሮች በጉዞ ላይ እያሉ እና በቆይታዎ ጊዜ ያልተጠበቀ ችግር ሲያጋጥምዎ ውሉን ሲገዙ ከኩባንያችን በተሰጠዎት አድራሻ ካሉበት ቦታ ሆነው በመደወል አስፈላጊውን እርዳታ ያገኛሉ፡፡