ከምህንድስና ጋር የተያያዙ የዋስትና ሽፋኖች (Engineering Insurance)

ይህ የዋስትና ሽፋን የተለያዩ የዋስትና ሽፋን ዓይነቶች ሲኖሩት ጥቂቶቹ የሚከተሉት ናቸው፡፡

  • የስራ ተቋራጮች መገልገያ መሳሪያዎች ዋስትና
  • የኮንትራክሽን ስራ ተቋራጮች ዋስትና
  • የማሽነሪ/ፋብሪካ ተከላ ዋስትና
  • የቦይለር ዋስትና
  • የኤሌክትሮኒክስ መሳሪያዎች ዋስትና
የኮንስትራክሽን ስራ ተቋራጮች ዋስትና

ማንኛውም ህንፃ ወይም ሲቪል ምህንድስና በአካል ጉዳት፣ በግንባታ ላይ ያሉ ስራዎችን በማውደም እና በቦታው ላይ ያሉ ማናቸውንም ጊዜያዊ ግንባታዎች፣ የተቋራጮች ፋብሪካዎች እና መሳሪያዎች ላይ በሚደርሱ አደጋዎች ላይ የሚሰራ የኢንጂነሪንግ መድን አይነት ነው። የማይንቀሳቀስ የግንባታ እና የሲቪል ምህንድስና ስራዎችን ለመሸፈን የተነደፈ ነው.

Image
የመሬት መንቀጥቀጥ ሁሉም ስጋቶች

ከግንባታው ፕሮጀክት አፈጻጸም ጋር ተያይዞ ለሚነሱት የማሽነሪዎች፣የእጽዋት እና የብረታብረት ግንባታዎች እንዲሁም የሶስተኛ ወገን የይገባኛል ጥያቄዎችን በተመለከተ አጠቃላይ እና በቂ ጥበቃ ያደርጋል።

Image
የኮንስትራክሽን መሳሪያዎች ዋስትና

ይህ ውል በተለያዩ ማሽነሪዎች ላይ ለሚደርስባቸው ጉዳት ሙሉ እና በቂ ሽፋን በሁሉም የግንባታ ቦታዎች ዋስትና ይሰጣል ፡፡

Image
የስራ ተቋራጮች መገልገያ መሳሪያዎች ዋስትና

የዚህ ውል መሰረታዊ ሐሳብ ለተለያዩ የኮንስትራክሽን ስራዎች ለሚውሉ ዕቃዎች በስራ ላይ ለሚደርስ ዉጫዊ ጉዳት በቂ እና ሙሉ ዋስትና መስጠት ነው ፡፡ ይህ ዋስትና በውጫዊ ምክንያት በሚመጣ ድንገተኛና ያልተጠበቀ አደጋ ሳቢያ በንብረት ላይ ለሚደርስ ጉዳት ዋስትና ይሰጣል ፡፡ ውሉ የዋስትና ሽፋን የሚሰጠው መሳሪያዎቹ በስራ ላይ እያሉና በተቀመጡበት ቦታ  ለሚደርስባቸው ጉዳት ነው ፡፡

Image
የማሞቂያ/የቦይለር ዋስትና

ይህ ውል ፋብሪካዎችና የተለያዩ ተቋማት የሚጠቀሙባቸው ማሞቂያ/ቦይለር ላይ የእሳት አደጋን ሳይጨምር ለሚደርስ ያልተጠበቀና ድንገተኛ አደጋ ዋስትና ይሰጣል ፡፡ ከዚህ በተጨማሪም 3ኛ ወገን ላይ ለሚደርስ አደጋ እንደአስፈላጊነቱ ሽፋን ሊሰጥ ይችላል ፡፡ በዚህ የዋስትና ዓይነት የማይሸፈኑ ክስተቶች ውሉ ላይ በዝርዝር ተጠቅሰዋል ፡፡

Image
የኤሌክትሮኒክስ መሳሪያዎች

ይህ የዋስትና ዓይነት በተለያዩ የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች ማለትም እንደ ኮምፒዩተር፣ ቴሌቪዥን፣ ሰርቨር እና በመሳሰሉት ላይ ለሚደርስ ያልተጠበቀና ድንገተኛ ጉዳት ዋስትና ይሰጣል ፡፡ 

Image

Similar blogs